News detail

Image Here

በፕላንና ልማት ሚንስቴርና ተጠሪ ተቋማት በአማራ ክልል ለተከናወነው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለተሳተፉ የቴክኒካል ኮሚቴ አመራሮችና ሰራተኞች የእውቅና መርሃ ግብር ተካሄደ። መጋቢት 5/2017 (ፕ.ል.ሚ - አዲስ አበባ)… See more

የፕላንና ልማት ሚንስቴርና ተጠሪ ተቋማት (የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ፓሊሲ ጥናት ኢኒስቲትዩት እና የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን) በጋራ በመቀናጀት በ2016 በጀት አመት በአማራ ክልል ዋግህምራ ዞን ሰቆጣ ከተማ የተከናወኑ የክረምት የበጎ ፈቃድ ተግባራት ለተሳተፉ የቴክኒካል ኮሚቴ አመራሮችና ሰራተኞች የእውቅና መርሃ ግብር ክንውን ማጠቃለያ ላይ የፕላንና ልማት ሚንስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ፍፁም አሰፋ እንደተናገሩት በአማራ ክልል ሰቆጣ ከተማ የተከናወነው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የመንግስትን የትኩረት አቅጣጫ መሬት ያስነካ ለቀጣይ ስራ መነሳሳት የሚፈጥር ከመሆኑ ባሻገር በተጠቃሚዎቹ ዜጎች ህይወት በተጨባጭ ትርጉም ያለው ለውጥ ያመጣ በመሆኑ ነው።

የተሰራውን ስራ ውጤት በመገምገም ሂደት ስኬታማ ከመሆኑ ባሻገር የተቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን የገለፁት ክብርት ዶ/ር ፍፁም በሰቆጣ ከተማ ለተከናወነው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተሳካው ስራው በተቀናጀና በተናበበ መንገድ በመመራቱ በመሆኑ በቴክኒክ ኮሚቴው ለተደረገው ጥረት የምስጋናና የእውቅና መርሃ ግብር መዘጋጀቱ ለቀጣይ ስራ መነሳሳት እንደሚፈጥር ጭምር አስረድተዋል።

ክብርት ሚኒስትሯ አክለውም አገልግሎቱ በተለይ ከፍተኛ ወጭ የሚጠይቁና የምህንድስና ስራዎች በውስጥ አቅም መሰራቱ ፣ በአስቸጋሪ ሁኔታዎችን በመቋቋም በአጭር ጊዜ መስራት መቻሉ ትምህርት ከሚወሰድባቸው ነጥቦች ዋናዎቹ መሆናቸውን ጠቁመው በቀጣይ በሚከናወኑ ተመሳሳይ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎች የተጠቃሚዎችን ዘላቂ ህይወት ባተኮሩ የልማት ስራዎችንና አዳዲስ ነገሮችን ያካተተ እቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባር እንደሚገባ ተናግረዋል።

በሰቆጣ ከተማ በተካሄደው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የአረንጓዴ አሻራ ልማት፣ የተማሪዎች ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ፣ የአቅመ ደካማ ነዋሪዎች መኖሪያ ቤት ግንባታ የማካሄድ እና ሌሎች ጊዜያዊና ዘላቂ ድጋፎች በቀዳሚነት የተሰሩ ስራዎች ሲሆኑ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ የተሳካው በተቀናጀ መንገድ በመመራቱ መሆኑ ተጠቁሟል።

recent News
  • Image Here

    በፕላንና ልማት ሚንስቴርና ተጠሪ ተቋማት በአማራ ክልል ለተከናወነው …

    01 May 2025
  • Image Here

    Minister of Planning and Development, H.E, Dr. Fitsum …

    01 May 2025
  • Image Here

    The steering Committee, which was established to conduct …

    01 May 2025