News detail

Image Here

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የፋይናንስ ተቋማት አየር ንብረት ለውጥን ለመከላለከል በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ እደሚገባ አስታወቀ። መጋቢት 04/ 2017 ዓ.ም (ፕ.ል.ሚ. - አ/አበባ)

ኢትዮጵያ የአየር ንበረት ለውጥን ለመከላከል በምታደርገው ጥረት የአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ የአፌድሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ፍጹም አሰፋ አሳሰቡ። ይህንንም ያሳሰቡት “የፋይናንስ ተቋሞቻችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የአየር ንብረት ፋይናንስ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል” በሚል መሪ ቃል ከሁሉም የፋይናንስ ተቋማት አመራሮች ጋር ዛሬ በተካሄደው የምክክር መድረክ ላይ ነው።

መንግስት የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም የሚያስችሉ ተጨባጭ ተግባር እያከናወነ ይገኛል ያሉት ሚኒስተሯ፤ ላለፉት ስድስት ዓመታት በውጤት የተጓዘው የአረንጓዴ አሻራ፥ ላለፉት ሶስት ዓመታት በርካታ ስኬቶች የተመዘገበበት የሌማት ትሩፋትና የበጋ ስንዴ ምርት ወጤታማ ስራ የተከናወነባቸው ዘርፎች መሆናቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል።

“ላለፉት አስርት ዓመታት የታዳሽ ሃይል ተግባራት በስፋት እየተሰራ የዘለቀው የዘላቂ መሬት አጠቃቀም፥ እምርታ የታየበት የኮሪደር ልማታችን የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋትና አረንጓዴ ልማት ለማረጋገጥ ያለንን ቁርጠኝነት ለሀገራችንም ሆነ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተግባር ያሰየንበትም ነው” ብለዋል ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ።

ስለሆነም የአየር ንብረት ለውጥ ፈተና መንግስት ብቻውን ሊወጣው የሚችለው ጉዳይ ስላልሆነ የተለያዩ የባለድርሻ አካላት ርብርብን የሚጠይቅ በመሆኑ የፋይናንስ ዘርፉ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ ለመቋቋም ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት እንዲደግፉ ጥሪ ቀርቧል።

የፋይናንስ ተቋማት ለአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ተጋላጭ በመሆናቸው ያላችውን ሃብትና እውቀት በተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስት በማድረግ እንዲሳተፉ መንግስት ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራ፣ ድጋፍም ያደርጋል ብለዋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር አቶ ስዩም መኮነን የሀገር ውስጥ ፋይናንስ ተቋማት ከአለም አቀፍ ፋይናንሰ ጋር ትስስር በመፍጠር ለአረንጓዴ ልማት ወይም አየር ንብረት ለውጥ አስተዋጽኦ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል። የፋይናንስ ተቋማት በአረንጓዴ ልማት ላይ ለተሰማሩ ባለሃብቶች ብድር እንዲያገኙ፣ ተቋማት ቀጣይነት ያለው የካርቦን ልቀት ቅንሳን ተግባራዊ እንዲያደርጉ እና በገንዘብም ድጋፍ እድታደርጉ መንግስት ፍላጎት አለው ብለዋል።”

በአረንጓዴ ልማት ላይ ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸውን የፋይናንስ ተቋማት መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግም በውይይቱ ላይ ተናግረዋል።

የፋይናንስ ተቋማቱም በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ላይ አስተጽኦ የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው በውይይቱ ላይ ተንፀባርቋል።

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የአየር ንብረት ለውጥ ሥራዎችን አካታችና አሳታፊ ለማድረግ ያስቀመጣቸውን ስትራቴጂክ ግቦችን ለማሳካት ከዋና ዋና ባለድርሻ አካላት ጋር ከለጋሽ ድርጅቶች፣ ከሲቪክ ማህበረሰብ አካላት፣ ከግሉ ዘርፍ፣ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተመሳሳይ መልኩ ከፋይናንስ ተቋማት ጋር ተከታታይ ውይይቶችን እያደረገና ቅንጅታዊ አሠራሮችን በከፍተኛ ደረጃ በመዘርጋት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።

recent News
  • Image Here

    በፕላንና ልማት ሚንስቴርና ተጠሪ ተቋማት በአማራ ክልል ለተከናወነው …

    14 March 2025
  • Image Here

    በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የፋይናንስ ተቋማት አየር ንብረት …

    13 March 2025
  • Image Here

    የዘላቂ ልማት ግቦችን ተግባራዊነት ለማጠናከር ባለሙያዎች ተቀናጅተው ሊሰሩ …

    13 March 2025