News detail

Image Here

የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡ አዲስ አበባ | ሚያዝያ 22 /2017

የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በጋራ በመሆን በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ውይይት አካሂደዋል፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶክተር ፍጹም አሰፋ በአገራችን ኢትዮጵያ ወቅታዊና ሀገራዊ የሆኑ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ ፓለቲካዊ እና በተለያዩ ዘርፎች ላይ በየጊዜው የሚደረጉትን ለውጦችና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ሁሉም የመንግስት ሠራተኞች በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እንደሚያስፈልግ እንዲሁም በዕውቀት ላይ ተመስርተው ስራቸውን በአግባቡ እንዲፈፅሙ ለማስቻል የተዘጋጀ የውይይት መድረክ መሆኑን አስታውቀዋል።

ክብርት ሚኒስትሯ ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት እና ሰባት ዓመታት በሀገራችን የመንግስት ለውጥ ካስተናገደች በኋላ የሚጨበጡ እና የሚታዩ ድሎች በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚ እና በፖለቲካ ዘርፎች ማምጣት እንደተቻለ አመላክተው ባለፉት ስድስት እና ሰባት ዓመታት ያስመዘገብናቸው መልካም ስራዎች ያሉብንን ትልልቅ የቤት ስራዎች እንዳያዘናጉን መጠንቀቅ አለብን ብለው ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡

በዕለቱ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ ወቅታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የውይይት ሰነድ አቅርበዋል፡፡ በቀረበውም ገለጻ ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታና ቀጣይ አቅጣጫ ላይ የተፈጠረውን ግንዛቤ መነሻ በማድረግ የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች የሚጠበቅባቸውን እንዲያደርጉ አቅጣጫ በማስቀመጥ የውይይት መድረኩ ተጠናቋል።

recent News
  • Image Here

    የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ …

    01 May 2025
  • Image Here

    International Consultation Forum on Climate Change Held in …

    01 May 2025
  • Image Here

    Educating for a Sustainable Future.

    01 May 2025