News detail

Image Here

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የፕላንና ልማት ማኒስቴር መንግስት የሴቶችን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እና ሁለንተናዊ ተሳትፎን ለማረጋገጥ በወሰደው ተከታታይና ጠንካራ እርምጃዎች አበረታች ለውጦች መመዝገባቸውን አስታወቀ። መጋቢት 10/2017 ዓ.ም (ፕ.ል.ሚ. - አ/አበባ)

መንግስት የሴቶችን መብት ለማስጠበቅ በፖለቲካዊ፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚ ረገድ ያላቸውን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም የአመራርነትና ውሳኔ ሰጭነት ሚናቸውን ለማሳደግ እየወሰደ ባለው ጠንካራ እርምጃ አበረታች ለውጦች ማስመዝገብ መቻሉን የኢፌድሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ፍጹም አሰፋ ገለጹ።

ክብርት ሚኒስትሯ ይሄን ያሉት በአለም ለ114ኛ በኢትዮጵያ ለ49ኛ ጊዜ በተቋም ደረጃ እየተከበረ የሚገኘዉ የአለም ሴቶች ቀን በተከበረበት ወቅት ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ነው።

በዓሉ "ፈጣንና ቀጣይነት ያለዉ ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል" በሚል መሪ ቃል ተከበሯል።

በኢትዮጵያ 50 በመቶ በላይ የሚሆነው የህዝብ ቁጥር የሚወክሉት ሴቶች መሆናቸውን የገለጹት ክብርት ዶ/ር ፍጹም ከቁጥር ባለፈ ሴቶች ትልልቅ አቅም ያላቸው በስራ ፈጣሪነት ማሳተፍ የአገራችንን እድገት ማፋጠን ያስፈልጋል ብለዋል።

በዓሉ የፆታ እኩልነትን በማስፈን ሴቶች ከነበረባቸው ድርብርብ ተጽዕኖ እንዲላቀቁና በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊና በፖለቲካዊ መስኮችም እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማስቻሉም በላይ ቀኑ ሴቶች በህብረተሰቡ ውሰጥ የሚገባቸውን እውቅናና ስፍራ እንዲገኙ አስችሏል ተብሏል።

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በሁሉም ዘርፍ የመጡ ለውጦችን ፈጣንና ቀጣይነት ባለው መልኩ ለመምራት የስርዓተ ፆታ እኩልነትን ለማስፈን የሚያስችሉ ስልቶችን በመንደፍና በስራ ላይ በማዋል ለተፈፃሚነቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ ክብርት ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም "ሴቶች ለአየር ንብረት ለውጥ ያላቸው ሚና" በሚል ርዕስ የውይይት ጽሑፍ የቀረበ ሲሆን ሴቶች የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል ትልቅ ድርሻ እንዳላቸው ተመላክቷል። በመድረኩ ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ እና የመሠረት የበጎ አድራጐት ድርጅት ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ የህይወት ልምዳቸውንና ተሞክሮዎቻቸውን አጋርተዋል።

recent News
  • Image Here

    በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የፕላንና ልማት ማኒስቴር መንግስት የሴቶችን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና …

    01 May 2025
  • Image Here

    Ministry of planning and development in collaboration with …

    01 May 2025
  • Image Here

    The Ministry of Planning and Development discussed with …

    01 May 2025